Description
“በጋራ መስራት እንጅ በጋራ ማሰብ አይቻልም። ብቻችሁን ሆናችሁ አስቡ ፣ ስራ ላይ ግን ተባበሩ!”
*
እድሜ ጊዜ ነው። ሰው ሞተ የሚባለውኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ሕመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው።
የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው “ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው።” እንዴት? የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የተቀንሰ ነውና።
*
” በዚህ አለም ላይ ስንኖር ታች የነበርንበት ከንቱ ይሆናል እየጨበጥን እንርግጣለን ክብር የሰጠነውን እናዋርዳለን። ከዚህ በላይ የለም ያልነውን ተራ ነገር እናደርገዋለን አለሙ እንደዚሁ ነው ንፋስ እንደመከተል ነው። የሚያርካ የሚያስደስት ምንም ነገር የለም።’
Reviews
There are no reviews yet.