የታንጉት ምስጢር

የታንጉት ምስጢር

የመጽሐፉ ርዕስ:- የታንጉት ምስጢር
ደሪሲ:- ብርሃኑ ዘርይሁን
የገፅ ብዛት:- 297
Category: Product ID: 2503

Description

‹‹. . . ኧረ ባባጃሌው!ምን አፈዘዘሽ?ነቃ እንድትይ ነበርኮ ያመጣሁሽ።”
“ይህንን እንዳይና እንድሰማ?”
“አዎና! አየሽ ቅማንቱም ፥ ወይጦውም ፥ አማራውም ሁሉም እግዜር የፈጠራቸው ሰዎች ናቸው። መልካቸው አይለይ!ወይ እነዚያ ጅራትና ቀንድ የላቸው። በስራም ፣ በሙያም የሆነ እንደሆነ አይተናነሱ። እኩል ሰርተው ያድራሉ።
እንዲያውም ወይጦዎቹና ቅማንቶቹ ይበልጣሉ በስራ። ዛዲያ ያቺ ልጅ እንዳየሻት ”ቅማንት ነሽ ወይ?“ብዬ ስጠይቃት ‘አይደለሁም’ እንዳትል መሆንዋን ታውቃለች። ’ነኝ’ እንዳትል ደግሞ አፈረችበት። ዝም ብላ መቅለስለስ ሀፍረትነቱን ገና ያላወቀው ትንሹ ልጅ ይሻላል። ስቆብኝ ሄዳ!
ያኛው ግን ‘ቅማንት ነህ ወይ?’ ብዬ ስጠይቀው አስተባበለኝ። አማራ ነህ ወይ ስለው ደግሞ ‘አወና !” አለኝ ተኩራርቶ. . .። ››
***
‹‹ታንጉት የኖረችው በሕፃንነቷ በገጠር፥ በኋላም፥ ባልዋ በዘመተበት፥ ቴዎድሮስ በሰፈረበት በየጫካው ስትዘዋወር ነው። ቀደም ሲል ያየችው ትልቅ የሕዝብ መኖሪያ ሠፈር ቢኖር፥ የጭልጋና የመተማ መንደሮች ነበሩ። እነርሱም በጊዜው አስደንቀዋት ነበር። የደረስጌ ጦርነት እንዳበቃ፥ ገብርዬ ቋራ ድረስ ገሥግሦ በመምጣት ጎንደር ይዙዋት ሲገባ ዐይንዋን ማመን አቃታት። ግንቦቹ፥ ሕንፃዎቹ በሰው እጅ የተሠሩ አልመስላት አለ። ራስዋ የለበሰችው ጥበብ ኩታና ቀሚስ የማያሳጣ ቢሆንም ከጎንደር ወይዛዝርት አለባበስ፥ ሹሩባ አሰራሩ፥ ጉትቻው፥ መስቀሉ፥ ሌላው ጌጣ ጌጥ ሁሉ ትንግርት ሆነባት። የካህናቱ ጥምጥም ሳይቀር ሌላ ነው። … ድንገት ከሰው መንደር ገብቶ እንደ ተደናገረ የዱር አውሬ አንዳች ዐይነት ፍርሃት ቢጤ ተሰማት።››
***
‹‹በገብርዬ የታማኝነት ስሜት በሕልም እንኳን መሸፈት ራሱ እንደ ክህደት የሚቆጠር ነበር፡፡ ይህንን ክህደት አንደ ደህና ነገር ለሰው ማውራት ደግሞ ከትዝብት ያለፈ ዓመፅ መስሎ ተሰማው፡፡ ሰው በሚጠላው ላይ ይሸፍታል፡፡ “የተበደለ ሰውም ቢያምፅ አይፈረድበትም፡፡” በሚወዱትና በሚታመኑት ላይ እንዴት ሲደረግ ይታሰባል? ገብርዬ ተራቅቆ ባይፈላሰፍም ማንም ሰው አንድ ጠቅላላ ሥርዓት መከተል እንደሚገባ ይሰማዋል፡፡ በጦር ሜዳ ደረቱን አስጥቶ ልቡን ሰጥቶ የሚዋጋውን ያህል አገር በመበጥበጥ፤ መንደር ለማመስ ለመዝረፍ ወይም ለመፈራትና ለመታወቅ የሚደረግ ሽፍትነትን በጣም ይጠላል፤ ይጠየፋል፤ ቴዎድሮስን ያመነበት ዋናው ምክንያትም ይኸው ነበር፡፡››
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “የታንጉት ምስጢር”

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Style switcher RESET
Body styles
Color settings
Link color
Menu color
User color
Background pattern
Background image