በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ

በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ

የመጽሀፉ ርዕስ:- በዓሉ ግርማ
ሕይወቱና ሥራዎቹ
በእንዳለጌታ ከበደ
Shipping Weight: 520 grams
Category: Product ID: 2852

Description

<<አሟሟቱ ብቻ ሳይሆን አኗኗሩም ምስጢራዊና በገድል የተሞላ እንደሆነ የሚነገርለት የበዓሉ ግርማን የሕይወት ታሪክ ለመጻፍ፣ ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ፣ በዓሉ ግርማ የተወለደበትን፣ ያደገበትን፣ የተማረባቸውንና የሠራባቸውን ተቋማት እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለበትን ቦታ ጭምር መዳሰሱ የታወቀ ሲሆን፣ የበዓሉን ቤተሰቦች፣ አብሮ አደጎች፣ የተማሪ ቤት ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ከፍተኛ የደርግ መንግሥት ባለሥልጣናትን ጭምር ቃለ መጠይቅ በማድረግ፣ የታተሙና ያልታተሙ ሰነዶችንም በመፈተሽ የሕይወት ታሪኩ የተሟላ እንዲሆን ጥረት አድርጓል፡፡
ሕይወቱና ልብወለዶቹ ያላቸውን ተዛምዶ በመቃኘትም የተደበቀና ሊገለጽ ይገባዋል ብሎ የሚያምንበትን የደራሲውን የሕይወት ክፍልም ተንትኗል፡፡
መጽሐፉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ አራት ዓመታት ፈጅቷል፡፡ ይህ ‹በዓሉ ግርማ፡- ሕይወቱና ሥራዎቹ› በሚል ርዕስ የታተመው የእንዳለጌታ ከበደ መጽሐፍ፣ ከ32 ዓመታት በፊት፣ የካቲት ወር በገባ በመጀመርያው ሣምንት እንደዘበት ወጥቶ የውሃ ሽታ ሆኖ መቅረቱን ለማመልከትና በአንባብያን ዘንድም ትውስታውን ለመጫር ሲባል፣ በቅርቡ መጽሐፍ ገበያ ላይ እንደሚውል ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የመጽሐፉ አከፋፋዮች ገልፀውልኛል፡፡
መጽሐፉ፣ በአጻጻፍ ቴክኒኩ፣ በመረጃ አጠቃቀሱና በሃሣብ አተናተኑ በጥንቃቄ የተሠራ እንደሆነ መጽሐፉ ለህትመት ከመቅረቡ በፊት ያነበቡት የሥነ ጽሑፍ ምሁራን የመሰከሩ ሲሆን፣ በዓሉን በሚመለከት ተሸፋፍነው የቀሩ የውልደቱ፣ የዕድገቱ፣ የትምህርቱ፣ የትዳሩ፣ የባለሥልጣንነት ዘመኑ፣ የሙያ ሕይወቱ፣ የእስር ቤት ቆይታውና የአገዳደሉ ሁናቴ በዝርዝር እንደቀረበም ተናግረዋል፡፡
እንዳለጌታ ከበደ ከአጫጭር ልብወለዶችና ከረጃጅም ልብወለድ ሥራዎቹ በተጨማሪ፣ ‹ማዕቀብ› በተባለው ስለጸሐፍትና መጻሕፍት በሚተርከው ኢ-ልብወለድ ሥራውና የቃቄ ውርድወት በተባለች ሴት ገድል ላይ በተመሰረተውና ‹እምቢታ› (2006) በተሰኘው ታሪካዊ ልብወለዱ የሚታወቅ ደራሲ ነው፡:>>
——————————–
ከመጽሐፉ ገጾች:-
“…እዚያ ውስጥ ከኩባ ሠልጥነው የመጡ ኮማንዶዎች አሉ። ኮማንዶዎቹ ቀስ ብለው ይጠጉንና ባልጠበቅነው ጊዜ ያልጠበቅነው ቦታችንን ይመቱናል። አሰቃቂ ነው አታያቸውም።… እናም ኮቴ ስሰማ እንደቆቅ ንቁ እንደቆቅ ስጉ እሆናለሁ። ያ ቀን የሠማሁት ኮቴ ግን የኮማንዶዎች አልነበረም። ዓይኔ በጨርቅ ታስሯል…ኮቶዎች ንቻ ሳይሆን ድምፅም ተሠማኝ። የሚያወረውን ሠው ለየሁት። ሀኪማችን ነው። ሀኪሙ “በዓሉ ግርማ አሁን ምንህን ነው የሚያምህ?” ሲለው ሠማሁ። ፈራሁ። ደነገጥኩ በዓሉ እዚህ ነው እንዴ ያለው? አልኩ ከሀገር ጠፍቷል ተገድሏል ተደብቋል የሚባለው ነገር ውሸት እንደሆነ አወቅሁ። በዓሉም “ሆዴን ነው የሚያመኝ” ሲል ሠማሁት። ሀኪሙ ምን ማድረግ እንዳለበት ይመስለኛል የሆነ ነገር እየነገረው ከአጠገቤ አለፉ። ከአጠገቤ እንዳለፉ አላስችል አለኝና ቀስ ብዬ ባልታሠረ እጄ ዓይኔ ላይ የተጋረደውን ጥቁር ጨርቅ ገለጥ አድርጌ አየኋቸው። ራሱ ነው – በዓሉ!..”
“ሚስት ከማግባቱ በፊት ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ገርል ፍሬንዱ ነበረች ፤ በጣም ይወዳት ነበር። እሷም እንዲሁ። ….እና ፣ራስ መኮንን ድልድይ፣ከድልድዩ ወደ አራት ኪሎ ስትሄድ፣በስተቀኝ በኩል፣ቤንዚን ማደያው ጋ ስትደርስ አንድ ግቢ ነበር፦እንደ ፔንሲዮንም አንደ ሆቴልም የሚያገለግል…”

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ”

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Style switcher RESET
Body styles
Color settings
Link color
Menu color
User color
Background pattern
Background image