Description
❝የሀገር እናቶች ትላንትን የሙጥኝ እንዳሉ ያዘግማሉ። ክሳዱን ጨምድደው ሊጥ በሚጠልቁበት ቅል አናት አናቱን ይቀውሩታል — “ጊዜ የሰጠው ቅል እንኳን ትላንትን ድንጋይ ይሰብራል”። ሮጠው ያልጠገቡ ልጆቻቸው መልኩን አይተውት ለማያውቁት ንጉሥ፤ ጎባጣ ይሁን ለግላጋ… ግራጫ ይሁን ቢጫ ለማይለዩት ርዕዮተ—ዓለም ሲሞቱ አይተዋል። ማኀፀናቸው ውስጥ ሲገላበጥ የረገጣቸው እግር ተቆርጦ ሲመለስ፤ በውስጣቸው የተላወሰ ገላ በሦስት ክንድ መሬት ውስጥ ሲረጋ አልቅሰው ሸኝተዋል። በሆዳቸው ውስጥ ተቀምጦ የተዋደደ አጥንት ሲከሰከስ፤ በሰውነታቸው ውስጥ የተቋለፈ ጅማትና ደምሥር በአንዲት አረር ዓይናቸው ሥር ታሪክ ሲሆን፤ ከዚያችም አረር ጀርባ ታጣፊ ክላሺንኮቭ፤ ከእርሱ ጀርባ ቃታውን የሳበች ጣት፤ ከእርሷ ጀርባ ሌላኛው ልጃቸው መኖሩን ተመልክተዋል። ለሞተው ልጃቸው ባማረሩበት አፍ፤ ገዳይ ሆኖ ለተረፈ ልጃቸው “ተመስገን” ይሉበታል።
–
|ከመጽሐፉ የተወሰደ]
Reviews
There are no reviews yet.