Description
“ያለጥንቃቄ ሰው ከእንስሳት ይበልጣል የሚል ማን ነው?”
*
“…ልክ እንደ ታቦቱ ሁሉ፤ ታሪክ እንደሚነግረን መሬቱም ደም ለምዶ ከሆነ፤ የምድሪቱ አኬልዳማነት ለምኖርባት ከተማ ለገነቴ ብቻ አይመስለኝም፡፡ ገነቴ እንደ ትእምርት ትሆናለች እንጂ መላ አገሪቱ የደም መሬት ናት…”
*
ከጦጣነት በዝግመት ተለውጠን በሁለት እግር ቆምን እንላለን እንጂ ልባችን ገና ካጎበጠበት ሊቃና እንኳን አላሰበም፡፡ እንደ አራዊት መንጋ ሁሉ ኅብረተሰቤ የተገነባው በበላይ እና በበታች ሥርዓት ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ፈጽሞ እኩል ልትሆን አትችልም፡፡ ከላይ መሆን ካልቻልክ ከታች ትገኛለህ ነው፡፡ ይሄን በየቤታችን በአርጩሜና በምላስ አለንጋ ያስተምሩንና ደጅ ስንወጣ የገባርና የጭሰኛ ግንኙነት ይኖረናል፡፡
Reviews
There are no reviews yet.