አቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)

አቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)

የመጽሐፉ ርዕስ :- አቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)
ፀሐፊ:- ፊታውራሪ ተክለ ሐዋርያት ተክለማርያም
አሳታሚ፡- አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ
Product ID: 2810

Description

“ለሥራ ያበረታኝ ያያቴ ምክር ነው:: ልቤን እየሰረሰረ እየገባ ሞራሌን ይደግፈኛል::”
*
“ነጻነት ከሌለ የአገር እና የወገን ፍቅር ከንቱ ነው “
*
“ላገርህ እንደእርሾ ትሆናለህ፡፡ እውነተኛውን ሥልጣኔ ለማግኘት በርታ ሳትሰለች መሥራት አለብህ፡፡ በተወረ የአውሮፓ መንግስቶች ያጠፏችኋል፡፡የዓለምን ህዝቦች በሙሉ አጥፍተዋል፤ አበላሽተዋልም፡፡እናንተንም አይተዋችሁም፡፡ የክርስቲያን ሕዝብ በአፍሪካ ውስጥ ከናንት በቀር ሌላ የለም፡፡ በታሪካችሁ ከአውሮፓውያኖች ትቀድማላችሁ፡፡ ዘራችሁ እንዳይጠፋ ለማድረግ ከመማር በቀር ሌላ መድኀኒት አይገኝላችሁም፡፡” እያለች የምትነግረኝ ምክር በየሰዓቱ እየታወሰኝ ስንፍናዬን ያባርርልኝ ነበር:: ታዲያ ሞራሌን እያነቃቃሁ ሰውነቴን እያሥገደድኩ እሠራለሁ፡፡”
*
“አገሬ በጣም ናፍቃኛለች፤ መቃረቤ እየተሰማኝ ሰውነቴ ሁሉ ተቀሰቀሰ፡፡ በጣም ነቃሁ፤ ራሴ ጋለ፤ ልቤ በሃይል እየነዘረ ስሜት በዛብኝ፡፡ በጀርባዬ ላይ ነርቮቼ ጅማቶቼ የሚበጠሱ መሰለኝ፡፡ እንቅልፍም አይወስደኝም ሌሊቱን ሁሉ ዐይኖቼ አያኖቼ ሳይከደኑ እንዳፈጠጡ አድራለሁ፡፡ ቀንም ብጋደም መገላበጥ ብቻ ሆነብኝ፡፡ እንደዚሁ ሦስት ቀናት እንደቆየሁ፣ ሰውነቴ ከልክ ያለፈ ስለነቃ ማሰብ ስላበዛሁ፣ ጤና አጣሁ፤ ድካም ተሰማኝ፡፡”
*
የተሰማ እሸቴ ባለሟልነት እየቀዘቀዘ የኔ እየጋለ ሄደ፡፡ ባለሟልነት አልወድም፤ ውርደት መስሎ ይታየኛል፡፡እኔ የምመኘው ለሀገሬ ጠቃሚ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ሌላ ትምህክት የለኝም፡፡እድገቴም የተመራው በዚሁ ዐይነት ብቻ ነው፡፡ አገልግሎቴም እገሌ ለተባለ ሰው ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያ ለጅምላነቷ እንዲጠቅም፣ ባለሟልነቴም የእገሌ መሆኑ ቀርቶ የብዛት እንዲሆን ነው፡፡
በመንግሥት ላይ ከፍተኛውን የሥልጣንና የመብት ደረጃ ስለያዙ፣ ረዳት እንድሆናቸው፣ በስሕተተኛ መንገድ እየተመሩ ለራሳቸውም ለኢትዮጵያም ጉዳት እንዳያመጡ፣ እድጠብቃቸው እንጂ፣ በዋዛ፣ በቀልድ፣ በውስልትና ላይ የተመሰረተ ባለሟልነት አያጓጋኝም፤ ከቶም ያስጠይፈኛል፡፡”
*
“ደጃዝማች ማናዬ እና ልጅ አስፋው (ልጃቸው) ሁለቱም ቆስለው ድንጋይ ተንተርሰው ተጋድመው አገኘናቸው። ልጅ አስፋው (በዃላ ፊታውራሪ) አወቀኝና ጠቀሰኝ። ዝም ብየው እንዳላየ ሰው ወደ ግንባር ሮጥኩ። ጦራችን ተደባልቋል። ሰውና ሰው አይተዋወቅም።…ሴቶች በገንቦ ውሃ እያዘሉ፤ በበቅሎዎቻቸው እንደተቀመጡ፤ ለቁስለኛ ውሃ ያቀርባሉ። ሲነጋገሩ ሰማዃቸው። ‘አረ በጣይቱ ሞት’ ይላሉ።…”
*
“ነጋሪቱ ከግንባርም ከጀርባም፤ ከቀኝም ከግራም ይጎሰማል። የተማረኩ ጣልያኖች አየሁ። ወዲያው ምርኮኞቹ በዙ። አንዳንዶቹ ወታደሮች፤ ሶስት ይበልጥም ጣልያኖች እየነዱ መጡ። በዃላ የምርኮኞች ብዛት ላይን የሚያሰለች ሆነ። ድል ማድረጋችንን አወቅሁት። ጣልያኖች መዋጋታቸውን ትተው ማርኩን እያሉ ይለምናሉ።”
*
“… ድንኳኑ ውስጥ ገባሁና መጋረጃውን ገለጥ አድርጌ አስተዋልኩ። ራስ (መኮንን) በርኖስ ለብሰው በሀዘን ተኮማትረዋል። ከሰራዊታቸው፤ ከንጉሱም ሰራዊት ስንት ሰዎች አልቀዋል። ፊታውራሪ ገበየሁ፤ ፊታውራሪ ተክሌ፤ ፊታውራሪ ዳምጠው፤ ቀኛዝማች ታፈሰ፤ ደጃዝማች ማናዬ፤ ፊታውራሪ ሃብተሚካኤል፤ ሌሎችም ስንቱ ሞተዋል …”

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “አቶባዮግራፊ (የሕይወቴ ታሪክ)”

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Style switcher RESET
Body styles
Color settings
Link color
Menu color
User color
Background pattern
Background image