Description
<<ይህ ጽሑፍ…ጠቃሚ የሆነ ሰነድ ነው ፤ ምክንያቱም እስከ አሁን የማናውቃቸውን ብዙ ነገሮች ስለሚያሳውቀን እና ከዚህ በፊት የምናውቃቸው ጉዳዮች ከሆኑም ስለሚያጠናክራቸው፣ ወይም ስለሚቃረናቸው ነው። መጽሐፉን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል። ክፍል አንድ እስከ ደርግ መቋቋም ድረስ ያለው የጸሐፊው ትውስታ ሲሆን፣ ክፍል ሁለት ደግሞ የደርግ ዘመን ይሆናል። ሁለቱም ዋጋ አላቸው። ሁለቱም ክፍሎች…ለታሪክ ተመራማሪው ብዙ መረጃ ይሰጣሉ። የመጀመሪያው ክፍል ማለትም ቅድመ ደርግ ለሁለተኛው ክፍል ታሪካዊ ዐውዱን (Historical context) ይሰጠዋል። በዚህ የተነሳ ኋላ ላይ ትላልቅ የፖለቲካ ወይም ወታደራዊ ሥልጣን ይዘው በሀገር ደረጃ ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦችን በወጣትነታቸው እናገኝበታለን። ጌታቸው ናደው፣ ደምሴ ቡልቶ፣ ተፈሪ ተክለሃይማኖት፣ ወዘተ…። ከጀነራሎችም ቢሆን አንዳንዶቹን ቀድመን እንተዋወቃቸዋለን። ለምሳሌ:- ጀሌራል አማን ሚካኤል አንዶም፣ ጀኔራል ነጋ ተገኘ ሊጠቀሱ ይችላሉ። ስለዚህ የመጀመሪያው እና ሁለተኛው ክፍል አንድ አምሳል ናቸው ማለት ይቻላል። የዚህ ትውስታ ትልቅ አስተዋፅኦ በስፋት መቅረቡ፣ ብዙ ጉዳዮችን በዝርዝር ማየቱ ነው።>> ~ ፕሮፌሰር ሽፈራው በቀለ
Reviews
There are no reviews yet.