Description
“…የእሳት እራት የብርሃን ግለትን ትወዳለች። ሥነ ተፈጥሮዋ ወደ ብርሃን እንድትሳብ ያስገድዳታል። እንደ ምልኪ በዙሪያው እያንዣበበች ትሄድና ትላተመዋለች። በትኵስነቱ ይፈጃታል። አትተወውም። ልክፍተኛው ነች። ትጠጋዋለች። እሱም አይምራትም። ደኅና አድርጎ ይልጣታል።
…የእሳት እራት ሞቷ የሚጀምረው ለብርሃን ካላት ፍቅር ነው። አንድን ሰው በስእብናው ብርሃናዊነት በጣም ልትወጂው እንደምትችይ ሲገባሽ ያኔ መፍራት አለብሽ። ህልውናሽ ራስሽን በማፍቀር ላይ ሳይሆን ሌላን ሰው በፍጹም ልብ ከመውደድ ከተነሣ አደገኛ ነው። አየሽ… ቢያጠፋም ብርሃን—ብርሃን ነው። አምርረሽ መጥላት አትችይም። ካለ እርሱ ሕይወትሽ ጨለማ እንደሆነ እንዲሰማሽ የማድረግ ትልቅ አቅም አለው። ብርሃንን መጥላት መቼ የዋዛ ሆኖ? እንደማፍቀሩ አይቀልም። ”
**********************
የመፅሐፉ ርዕስ : ትዝታሽን ለእኔ : ትዝታዬን ለአንቺ
ደራሲ:- እሱባለው አበራ ንጉሤ
የገጽ ብዛት:- 180
Reviews
There are no reviews yet.